1.1 KiB
1.1 KiB
ግብዝ፣ ግብዝነት
“ግብዝ” የሚለው ልቡ ክፉና ጠማማ ሆኖ በሰዎች ፊት ግን መልካም ሰው መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው ነው። “ግብዝነት” መልካምና እውነተኛ መስሎ ለመታየት አንድ ሰው የሚያደርገው ነው።
- ግብዝ ሰው ሰዎች ጥሩ ሰው ነው ብለው እንዲያስቡ መልካም ነገር ሲያደርግ የሚታይ ነው።
- ብዙውን ጊዜ ግብዞች እነርሱ ራሳቸው የሚያደርጉትን ክፉ ነገር ሌሎች ሲያደርጉ ይነቅፋሉ።
- አንዳንድ ልብሶችን መልበስን፣ አንዳንድ ምግቦችን መመገብን ወይም አለመመገብን የመሳሰሉ ሃይማኖታዊ ነገሮችን ቢያደርጉም ለሰዎች ግን መልካም ያልነበሩ ፈሪሳውያንን ኢየሱስ ግብዞች ብሏቸዋል።
- ግብዝ ሰው የሌሎች ሰዎች ደካማነት ላይ ጣቱን ይጠቁማል፤ የራሱን ደካማነት ግን አይቀበልም።