am_tw/bible/other/veil.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መሸፈኛ
“መሸፈኛ” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ራስን ለመሸፈን የሚያገለግለውን በጣም ስስ ልብስ ሲሆን፣ ራስና ፊት እንዳይታይ ይከልላል።
* ያህዌ ፊት ከነበረ በኋላ እስራኤል የፊቱን ብርሃን እንዳያዩ ለመጋረድ ሙሴ ፊቱን በመሸፈኛ ሸፍኖ ነበር።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴቶች ሕዝብ ባለበት ወይም ወንዶች ባሉበት ቦታ ሲሆኑ ራሳቸውንና ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር።
* “ሸፈነ” የሚለው ግሥ አንድን ነገር እንዳይታይ አደረገ ማለት ነው።
* አንዳንድ ትርጕሞች ቅድስተ ቅዱሳን መግቢያ ላይ ያለውን ግዙፍ መጋረጃ፣ “መሸፈኛ” ብለውታል። ይሁን እንጂ፣ እዚህ ላይ የሚያመለክተው በጣም ከባድ፣ ወፍራምና ግዙፍ ጨርቅ በመሆኑ፣ “መጋረጃ” የሚለው ቃል የበለጠ ትክክል ነው።