9 lines
1.1 KiB
Markdown
9 lines
1.1 KiB
Markdown
|
# ቤተ መቅደስ
|
||
|
|
||
|
ቤተ መቅደስ እስራኤል ለጸሎትና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሰበሰቡበት ዙሪያውን በተከበበ አደባባይ ውስጥ ያለ ሕንፃ ነው። ቤተ መቅደስ የነበረው ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ባለው የሞሪያ ተራራ ነበር።
|
||
|
|
||
|
* አብዛኛውን ጊዜ፣ “ቤተ መቅደስ” የሚለው ቃል ዋናውን ሕንፃ የሚከብባትን አደባባዮች ጨምሮ መላውን ሕንፃ ያመለክታል። አንዳንዴ የሚያመለክተው ውስጡ የሚፈጸመውን አምልኮ ሳይሆን ሕንፃውን ብቻ ነው።
|
||
|
* የቤተ መቅደስ ሕንፃ ቅድስትና ቅድስተ ቅዱሳን የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት።
|
||
|
* ቤተ መቅደሱ የእርሱ ማደሪያ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ተናግሯል።
|
||
|
* መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ከመኖሩ የተነሣ በክርስቶስ ያመኑ ሰዎች “የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ” ተብለው ተጠርተዋል።
|