am_tw/bible/other/thresh.md

10 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መውቂያ፣ መውቃት
“መውቂያ” እና፣ “መውቃት” የተሰኙት ቃሎች የስንዴን ዘር ከተቀረው የስንዴው ክፍል የመለየት ሥራን ያመለክታሉ።
* ገለባውንና አበቁን ከስንዴው መለየት እንዲቻል የሚወቃው እህሉ በመጀመሪያ በዱላ ይደበደባል፤ ወይም በሬዎች እንዲረማመዱበት ይደረጋል። ከዚያም ገለባው በነፋስ እንዲወሰድና እሁሉ ዐውድማው ላይ እንዲወድቅ እህሉና ገለባው ወደ አየር ይበተናል።
* “ዐውድማ” እህል ለመውቃት የሚያገለግል ትልቅና ሰፊ ቦታ ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበረው ዐውድማ ሰፊና ዝርግ ዐለት ወይም እህሉን በመውቃት ከገለባው መለየት እንዲቻል ሰፊና በጣም የተጠቀጠቀ መሬት ነበር።
* እህሉን በመደፍጠጥ ከገለባ ለመለየት፣ “መውቂያ ሰረገላ” ወይም፣ “መውቂያ መንኮራኩር” ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
* እህሉን መለየት እንዲቻል፣ “መውቂያ መዶሽ” ወይም፣ “መውቂያ ጣውላ” ጥቅም ላይ ይውል ነበር። ይህ የሚሠራው ከእንጨት ጣውላ ሲሆን በየጫፎቹ የሾሉ ብረቶች ነበርት።