am_tw/bible/other/raise.md

13 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መነሣት፣ ተነሣ
በአጠቃላይ፣ “መነሣት” “ብድግ ማለት” ወይም፣ “ወደ ላይ መውጣት” ማለት ነው።
* ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር፣ “ተነሥ” ማለት አንድ ነገር ወደ መገኘት እንዲመጣ ወይም እንዲታይ ማድረግ ማለት ነው። አንዳች ነገር እንዲያደርግ ሰውን መሾም ማለትም ይሆናል።
* አንዳንዴ፣ “ተነሥ” ማለት፣ “መመለስ” ወይም “እንደ ገና መሠራት” ማለትም ይሆናል።
* “ከሞት ተነሣ” የሚለው ሐረግ ውስጥ ያለው፣ “ተነሣ” ልዩ ትርጕም አለው፤ የሞተው ሰው እንደ ገና ወደ ሕይወት ሲመጣ ማለት ነው፥
* አንዳንዴ፣ “መነሣት” - አንድን ሰው ወይም ነገር ወደ ላይ ከፍ ማድረግን ያመለክታል።
* መነሣት፣ ተነሣ፣ “ወደ ላይ መሄድ” ማለትም ይሆናል።
* አንድ ሰው ወደ አንድ ቦታ ለመሄድ ከተነሣ፣ “ተንሥቶ ሄደ” ወይም፣ “ብድግ ብሎ ሄደ” ማለት ነው።
* አንድ ነገር፣ “ተነሣ” ከተባለ፣ “ሆነ” ወይም፣ “መሆን ጀመረ” ማለት ነው።
* ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሣ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤ ኢየሱስ ከሞተ ሦስት ቀን በኋላ መልአኩ፣ “ተነሥቶአል!” አለ።