am_tw/bible/kt/judge.md

11 lines
1.6 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ፈራጅ፣ ፍርድ
ብዙውን ጊዜ፣ “ፈራጅ” ወይም፣ “ፍርድ” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት ከግብረ ገብ አንጻር አንድ ነገር ትክክል መሆን አለመሆኑን በተመለከተ ውሳኔ መስጠት ነው።
* “የእግዚአብሔር ፍርድ” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው እርሱ ኀጢአት በሚለው ሰው ወይም ነገር አስመልክቶ ፍርድ ለማሳለፍ የሚያደርገውን ውሳኔ ነው።
* ሁሌም ቢሆን የእግዚአብሔር ፍርድ በኀጢአታቸው ሰዎችን መቅጣቱን ይጨምራል።
* “መፍረድ” የሚለው ቃል፣ “መኮነን” ማለት ሊሆንም ይችላል። በዚህ መልኩ ማንም ላይ እንዳይፈርዱ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ተናግሯል።
* ሌላው ትርጉም፣ በሰዎች መካከል በሚፈጠር ክርክር የትኛው ትክክል የትኛው ስሕተት እንደሆነ፣ “በሁለቱ መካከል መዳኘት” ማለት ነው።
* በአንዳንድ ዐውዶች መሠረት የእግዚአብሔር፣ “ፍርድ” እርሱ ትክክልና እውነት ብሎ የወሰነው ማለት ነው። በዚህ መልኩ ሲቀርብ ከእርሱ ሕግ፣ ደንብ ወይ ሥርዓት ጋር አንድ ዐይነት ትርጉም ይኖረዋል።
* “ፍርድ” ማስተዋል ያለበት ውሳኔ የማድረግ ችሎታን ያመለክታል። “ፍርድ” የሌለው ሰው ማስተዋል ያለበት ችሎታ የመወሰን ትበብ የሌለው ማለት ነው።