am_tw/bible/kt/faithful.md

8 lines
795 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ታማኝ፣ ታማኝነት
ለእግዚአብሔር፣ “ታማኝ” መሆን ዘወትር በእርሱ ትምህርት መኖር ማለት ነው። ለእርሱ በመታዘዝ እውነተኛነትን ማሳየት ማለት ነው ታማኝ ሆኖ የመገኘት ሁኔታ፣ “ታማኝነት” ይባላል።
* ታማኝ የሆነ ሰው ሁሌም ቃሉን እንደሚጠብቅና ለሌሎች ያለበትን ኅላፊነት ሁሌም እንደሚወጣ እምነት ሊጣልበት ይችላል።
* ታማኝ ሰው ረጅምና አስቸጋሪ ቢሆንበት እንኳ በጀመረው ሥራ ይተጋል።
* ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ዘወትር እግዚአብሔር እንድናደርግ የፈለገውን በማድረግ መጽናት ነው።