am_tw/bible/kt/blasphemy.md

8 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ስድብ፣ ተሰደበ
መጽሐፍ ቁስ ውስጥ፣ “ስድብ” እግዚአብሔርንና ሰውን በጣም በሚያንቋሽሽ መንገድ መናገርግን ያመለክታል። አንድን ሰው፣ “መስደብ” ሰዎች ሐሰት የሆነ መጥፎ ነገር እንዲያስቡ በዚያ ሰው ላይ ክፉ ነገር መናገር ማለት ነው።
* ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን መሳደብ ሲባል እርሱን ማማት ወይም እርሱን በተመለከተ እውነት ያልሆነ ነገርን በመናገር መሳደብን ወይም እርሱን በማያስከብር ሁኔታ ውስጥ መኖርን ያመለክታል።
* አንድ ሰው እግዚአብሔር ነኝ ቢል ወይም ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ሌላ እግዚአብሔር እንዳለ ቢናገር ያ ሰው ተሳድቦአል።
* አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች ሰዎችን ስለ መሰደብ የሚያመለክት ከሆነ ይህን “ሐሜት” በማለት ተርጕመውታል።