በአዳም ኃጢያት የተነሳ ምን ሆነ? ከእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ የተነሳ ምን ሆነ?
ከአዳም ኃጢያት የተነሳ የኩነኔ ፍርድ ሆነ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ የተነሳ ጽድቅ ሆነ። [5:16]
አዳም ኃጢያት ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ምን ነገሰ? በእግዚአብሔር የጽድቅ ስጦታ የተነሳ ምን ነገሰ?
ከአዳም ኃጢያት የተነሳ ሞት ነገሰ፤ የእግዚአብሔርን ነጻ ስጦታ የሚቀበሉት በኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ህይወት ይነግሳሉ። [5:17]