ይህንን መጽሐፍ የጻፈው ማነው? የጻፈውስ ለማን ነው?
ይህንን መጽሐፍ የጻፈው ዮሐንስ ሲሆን የጻፈው በእስያ ለሚገኙ ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ነው [1:4]
ዮሐንስ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጠው ሦስት ስሞች የትኞቹ ናቸው?
ዮሐንስ ለኢየሱስ ክርስቶስ የታመነ ምስክር፣ ከሙታን በኩር፣ እና የምድር ነገሥታት ገዥ የሚል ስም ይሰጠዋል [1:5]
ኢየሱስ አማኞችን ምን አደረጋቸው?
ኢየሱስ አማኞችን መንግሥትና የእግዚአብሔር አብ ካህናት አደረጋቸው [1:6]