1.2 KiB
1.2 KiB
የተባረኩ ሰዎች የሚታዩት የት ነው?
በጽዮን በእግዚአብሔር ፊት ይታያሉ፡፡ [84: 7]
ጸሐፊው ጸሎቱን እንዲሰማው የሚፈልገው ማን ነው?
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎቱን እንዲሰማው ይፈልጋል፡፡ [84:8]
ጸሐፊው የሚናገረውን እንዲሰማው የሚፈልገው ማንን ነው?
የያዕቆብ አምላክ የሚናገረውን እንዲሰማው ይፈልጋል፡፡ [84: 8]
ጸሐፊው እግዚአብሔር እንዲጠብቅላቸውና ስለማንስ ግድ እንዲለው ይፈልጋል?
እግዚአብሔር ጋሻቸውን እንዲጠብቅላቸውና ለቀባው ሕዝብ ግድ እንዲለው ይፈልጋል፡፡ [84: 9]
በእግዚአብሔር አደባባይ አንድ ቀን ከምን ይሻላል?
በእግዚአብሔር አደባባይ አንድ ቀን በሌላ ስፍራ ከሚያልፍ አንድ ሺህ ዓመት ይሻላል፡፡ [84:10]
ጸሐፊው በክፉዎች ድንኳኖች ውስጥ ከመኖር ይልቅ በአምላኩ ቤት ውስጥ ምን መሆን ይመርጣል?
እርሱ በአምላኩ ቤት በር ጠባቂ መሆንን ይመርጣል፡፡ [84:10]