ዳዊት ያልሸሸገው ምንድን ነው?
በልቡ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ፣ እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ታማኝ መሆኑን እና በሁሉ ነገር የእግዚአብሔርን ታማኝነት ከጉባዔው አልሸሸገም፡፡ [40:10]
ዳዊት እግዚአብሔር ምን እንዲያደርግለት ይጸልያል?
እግዚአብሔር ከዳዊት ምህረቱን እንዳይመልስ ነገር ግን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታማኝነት እና አስተማማኝነቱ ለዳዊት ሁልጊዜ የተጠበቁ እንዲሆኑ ይጸልያል፡፡ [40፡11]