ጸሐፊው የእግዚአብሔርን ቃል እና ድርጊት እንዴት ይገልጻል?
የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነው የሚሠራውም ነገር ሁሉ መልካም ነው። [33: 4]
እግዚአብሔር ምን ይወድዳል?
እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል። [33: 5]
በእግዚአብሔር ቃል የተሠራው ምንድን ነው?
ሰማያት በእግዚአብሔር ቃል ተሠርተዋል። [33: 6]
በእግዚአብሔር አፍ እስትንፋስ የተሠራው ምንድን ነው?
ከዋክብት ሁሉ በእግዚአብሔር እስትንፋስ ተሠርተዋል። [33:6]