am_tq/num/22/21.md

1.0 KiB

በለዓም በማለዳ ምን አደረገ?

በለዓም ተነሳ፣ አህያውን ጫነ፣ እናም በማለዳ ተነስቶ ከሞአብ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡

የእግዚአብሔር ቁጣ የነደደው ለምንድን ነው?

የእግዚአብሔር ቁጣ የነደደው በለዓም ከእነርሱ ጋር ስለሄደ ነው፡፡

የያህዌ መልአክ ምን አደረገ?

የያህዌ መልአክ በለዓምን ተቃውሞ በመንገዱ ላይ ቆመ፡፡

የበለዓም አህያ በመንዱ ላይ ምን ቆሞ አየች?

የበለዓም አህያ የያህዌ መልአክ የተመዘዘ ሰይፉን በእጁ ይዞ በመንገድ ላይ መቆሙን አየች፡፡

የበለዓም አህያ የያህዌን መልአክ ስትመለከት ምን አደረገች፣ በለዓምስ በአህያው ላይ ምን ፈጸመ?

የበለዓም አህያ ከመንገዱ ዘወር ብላ ወደ እርሻ ገባች፤ በለዓም አህያይቱን ወደ መንገዷ ለመመለስ መታት፡፡