በዘሪው ምሳሌ ውስጥ በእሾሃማ ተክሎች መካከል የተዘራው ምን ዓይነት ሰውን የሚወክል ነው?
በእሾህ መካከል የተዘራው ዘር ቃሉን የሚሰማ፣ ነገር ግን የዚህ ዓለም ጉዳዮች እና የብልጥግና ማታለል ቃሉን አንቆ የሚያስቀርበት ነው። [13:22]
በዘሪው ምሳሌ ውስጥ በመልካም መሬት ላይ የተዘራው ምን ዓይነት ሰውን የሚወክል ነው?
በመልካም መሬት ላይ የተዘራው ዘር ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውለው፣ ከዚያም ፍሬ የሚያፈራበት ሰው ነው። [13:23]