816 B
816 B
በዲያቢሎስ እንዲፈተን ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ የመራው ማን ነው?
በዲያቢሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ወደ ምድረበዳ መራው። [4:1]
ኢየሱስ በምድረ በዳ ለምን ያክል ጊዜ ጾመ?
ኢየሱስ በምድረ በዳ ለአርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ። [4:2]
ዲያቢሎስ ለኢየሱስ ያቀረበው የመጀመሪያው ፈተና ምን ነበር?
ዲያቢሎስ ኢየሱስ ድንጋዩን ወደ ዳቦ እንዲቀይር ፈተነው። [4:3]
ኢየሱስ ለመጀመሪያው ፈተና ምን መልስ ሰጠ?
ኢየሱስ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም አለ። [4:4]