am_tq/luk/21/20.md

691 B

የኢየሩሳሌም ጥፋት መቃረቡን የሚያመለክት ምንድነው?

ኢየሩሳሌም በጦር ሰራዊት ስትከበብ ጥፋቷ መቃረቡን ያመለክታል፡፡

የኢየሩሳሌም ጥፋት መቃረቡን ሲያዩ ሰዎች ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የተናገረው?

ወደ ተራሮች እንዲሸሹ፣ ከከተማ እንዲወጡ፣ ወደ ከተማይቱ እንዳይገቡ ነበር የተናገረው፡፡

ኢየሩሳሌም የምትጠፋበትን ቀን ኢየሱስ ምን በማለት ነበር የጠራው?

የተጻፈው ሁሉ የሚፈጸምበት የበቀል ቀን ነበር ያለው፡፡