am_tq/jer/35/05.md

983 B

የሬካባውያን ነገዶች ይጠጡ ዘንድ ወይን ጠጅ ሲሰጣቸው ምላሽ የሰጡት እንዴት ነበር?

ሬካባውያን እንዲጠጡ ወይን ጠጅ ሲሰጣቸው መጠጣት አልፈቀዱም፡፡

ሬካባውያን ወይን ጠጅ ለመጠጣት ያልፈቀዱት ለምንድን ነው?

ሬካባውያን አንዳች የወይን ጠጅ ለመጠጣት ያልፈቀዱት አባታቸው የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ‘አንዳች የወይን ጠጅ እናንተም ሆናችሁ የእናንተ ትውልዶች ለዘለአለም እንዳትቀምሱ` ብሎ ስላዘዛቸው ነው፡፡

ኢዮናዳብ ሬካባውያንን ቤት እንዳይገነቡ፣ ዘር እንዳይዘሩ፣ ወይም ወይን እንዳይተክሉ ያዘዛቸው ለምንድን ነው?

ኢዮናዳብ ይህንን ትዕዛዝ የሰጣቸው በድንኳን በድንኳን መኖር ስለነበረባቸው ነው፡፡