am_tq/gen/30/37.md

892 B

የያዕቆብን ደሞዝ በሚመለከት ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነበር?

ላባ፣ መንጋውን እንዲጠብቅለት ለያዕቆብ ከመስጠቱ በፊት በመጀመሪያ የያዕቆብ ድርሻ መሆን የሚገባቸውን እንስሶች ለይቶ አስቀራቸው

ያዕቆብ፣ ሽመልመሌ አድርጎ የላጣቸው በትሮች ምን ዓይነት ነበሩ?

ያዕቆብ ልብን፣ ለውዝ፣ ኤርሞን የሚባሉ እንጨቶችን ቅርንጫፍ በመላጥ ሽመልመሌ መልክ እንዲኖራቸው አደረገ

ያዕቆብ በሽመልመሌዎቹ በትሮች ምን አደረገ?

ያዕቆብ መንጋው ውሃ ለመጠጣት በሚመጡበት ጊዜ በፊት ለፊታቸው በውሃ ማጠጫ ገንዳው ውስጥ ሽመልመሌዎቹን በትሮች አስቀመጣቸው