ቃሉን የሚማር ሰው ከአስተማረው ጋር ምን ማድረግ አለበት?
ቃሉን የተማረ ሰው መልካምን ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ጋር ማካፈል አለበት። [6:6]
አንድ ሰው በመንፈስ በሚዘራው ዘር ምን ይሆናል?
ሰው በመንፈስ የሚዘራውን ያጨዳል። [6:7]
ለራሱ ስጋ የሚዘራ ሰው ምን ያጭዳል?
ለራሱ ስጋ የሚዘራ ሰው ከራሱ ስጋ መበስበስን ያጭዳል። [6:8]
በመንፈስ የሚዘራ ሰው ምን ያጨዳል?
በመንፈስ የሚዘራ ሰው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት የጭዳል። [6:8]