ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ማንም ሰው ምን ይሆንበታል?
ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ያ ሰው ከእስራኤል ተለይቶ መጥፋት አለበት፡፡ [ 12: 15]
በሰባቱ እርሾ የለሽ ቀናት እስራኤላውያን መሥራት የሚችሉት ብቸኛ ሥራ ምንድን ነው?
በእነዚህ ቀናት ለሁሉም የሚበሉትን ከማብሰል በስተቀር ምንም ሥራ አይሠራም፡፡ [ 12: 16-17]