am_tq/est/04/06.md

786 B

መርዶክዮስ ለሀታክ የነገረው ምንድን ነው?

መርዶክዮስ ለሀታክ የነገረው የደረሰበትን ነገር ሁሉ፣ እንዲሁም ሐማ የአይሁድን ሕዝብ ለማጥፋት ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማግባት ቃል የገባውን የገንዘብ ልክ ጭምር ነው። [4፡7]

መርዶክዮስ አይሁድን ለማጥፋት በሱሳ የወጣውን የዋናውን ዐዋጅ ቅጅ ለሀታክ የሰጠው ለምንድን ነው?

መርዶክዮስ ይህን ያደረገው ሀታክ ለአስቴር እንዲያሳያትና ወደ ንጉሡ ዘንድ ገብታ ስለ ሕዝቧ ምሕረት የመጠየቅንና የመማለድን ኃላፊነት እንዲያስጨብጣት ነው። [4፡8-9]