ዳንኤል አዋጁ ተፈርሞበት እንደ ጸና ካወቀ በሁዋላ ምን አደረገ?
ወደ ቤቱ ሄደ በጒልበቱ በመንበርክኮ ከአሁን በፊት ያድርገው እንደነበረ ጸለየ አምላኩንም እያመሰገነ።[ 6:10-12]
በዳንኤል ላይ የሚያሴሩ ሰዎች ዳንኤል ወደአምላኩ በሚጸልይበት ጊዜ ዳንኤልን ምን አደረጉ?
ሰዎቹም ወደንጉሱ ገብተው ዳንኤል አንተን አያከብርህም፤ ፈርመህበት የወጣውንም ዐዋጅ በመጣስ በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል አሉት።[ 6:13]