am_tq/1co/08/11.md

989 B

የጣዖትን ከንቱነት የተረዱ ጥንቃቄ ባለ ማድረግ ነጻነታቸውን ሲጠቀሙበት ደካማ ኅሊና ያለው ወንድም ወይም እኅት ምን ይሆናሉ?

ደካማ ኅሊና ያላቸው ወንድም ወይም እኅት ይጠፋሉ፡፡

በደካማ ኅሊናቸው ምክንያት ሆን ብለን በክርስቶስ ወንድም ወይም እኅት የሆኑትን ብናሰናክል ኀጢአት ያደረግነው ማን ላይ ነው?

ያሰናከልናቸው ወንድም ወይም እኅት ላይ ኀጢአት እናደርጋለን፤ በክርስቶስ ላይ ኀጢአት እናደርጋለን፡፡

ምግብ ወንድሙን ወይም እኅቱን የሚያሰናክል ከሆነ ጳውሎስ ምን እንደሚያደርግ ነው የሚናገረው?

ምግብ ወንድሙን ወይም እኅቱን የሚያሰናክል ከሆነ ጳውሎስ ከእንግዲህ ሥጋ እንደማይበላ ይናገራል፡፡