am_tn/rom/08/28.md

44 lines
1.9 KiB
Markdown

# አያያዥ ዐረፍተ ነገር
ጳውሎስ ክርስቲያን አማኞችን ከእግዚአብሔር ፍቅር ማንም ሊለያቸው እንደማይችል ያስታውሳቸዋል።
# ለተጠሩት
በሌላ አተረጓጎም፣ "እግዚአብሔር ለመረጣቸው"
# አስቀድሞ ላወቃቸው
"ገና ሳይፈጥራቸው እንኳ ላወቃቸው”
# መጨረሻቸውንም ደግሞ አስቀድሞ ወሰነ
"መዳረሻቸውን ደግሞ ወሰነ" ወይም "ደግሞም አስቀድሞ አቀደ"
# የልጁን መልክ እንዲኖራቸው
እግዚአብሔር ከፍጥረት ጅማረ አስቀድሞ በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ የሚያምኑት ኢየሱስን ወደ መምሰል እንዲያድጉ አቀደ። በሌላ አባባል፣ "ልጁን እንዲመስሉ ልለውጣቸው"
# ልጅ
ይህ ለኢየሱስ ለእግዚአብሔር ልጅ አስፈላጊ ማዕረግ ነው።
# እሱ የመጀመርያ ልጅ እንዲሆን
“ልጁ የመጀመርያ ልጅ እንዲሆን”
# ከብዙ ወንድሞች መካከል
እዚህ ላይ "ወንድሞች" የሚለው ሁሉንም አማኞች ወንድንም ሆነ ሴት ያመለክታል። በሌላ አባባል፣ "የእግዚአብሔር ቤተሰብ ከሆኑት ከብዙ ወንድሞችና እህቶች መካከል"
# መጨረሻቸውን አስቀድሞ ለወሰነላቸው
"እግዚአብሔር አስቀድሞ ዕቅድ ላወጣላቸው"
# እነዚህን ደግሞ ከጥፋተኝነት አወጣቸው
እዚህ ላይ "ከጥፋተኝነት አወጣቸው" የሚለው ያለፈውን ጊዜ አመልካች መሆኑ ይህ በእርግጠኝነት እንደሚሆን አስረግጦ ለመግለጽ ነው። በሌላ አባባል፣ "እነዚህን ደግሞ በፊቱ ከጥፋተኝነት ነፃ አደረጋቸው"
# እነዚህን ደግሞ አከበራቸው
x