am_tn/psa/073/001.md

28 lines
2.0 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ፡-
ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)
# የአሳፍ መዝሙር
“ይህ አሳፍ የጻፈው መዝሙር ነው፡፡” ይህ በ መዝሙረ ዳዊት 53:1 ላይ አንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡
# እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ
ዘማሪው የሚናገረው እግዚአብሔርን መታመን አንዳልቻለና በሚያዳልጥ መንገድ ሲራመድ ሊወድቅ እንደደረሰ አድርጎ ራሱን በማሰብ ሀጢአት ለመስራት እንደፈለገ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በእግዚአብሔር መታመን ለማቆም ደርሼ ነበር፤ በእርሱ ላይ ትልቅ ሀጢአት ለመስራትና በደለኛ ለመሆን ደርሼ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
# በአመፀኞች ቀንቼ ነበር
“አመፀኞች ቀናሁባቸው” ወይም “አመፀኞች ሰዎች የነበራቸው መልካም ነገር እንዲኖራቸው አልፈልግም”
# አመፀኞች
“አመጸኞች” የሚለወ ቅፅል እንደ ስም ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አመፀኞች ሰዎች” (የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)
# የክፉዎች ባለጠግነት
“ባለጠግነት” የሚለው ቃል እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉዎች በጣም ብዙ መልካም ነገር እንዳላቸው አይቼ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
# ክፉዎች
“ክፉዎች” የሚለው ቅፅል እንደ የስም ሀረግ ሊተረጎም ይቸላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች” (የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)