am_tn/pro/25/18.md

901 B

በጎረቤቱ ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው በጦርነት ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዱላ፣ ሰይፍ ወይም የተሳለ ቀስት ነው

ሐሰተኛ ምስክር ሰዎችን ከሚጎዱ ወይም ከሚገድሉ ከሶስት መሳርያዎች ጋር ተነጻጽሯል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በችግር ጊዜ የታመንከው ወስላታ ሰው እንደ ተበላሸ ጥርስ ወይም እንደሚያነክስ እግር ነው

ሞኝ ሰው ለሰው ችግር ከሚፈጥር የሰውነት ክፍል ጋር ተነጻጽሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በችግር ጊዜ ወስላታ ሰውን መታመን እንደ ተበላሸ ጥርስ ወይም እንደሚያነክስ እግር ችግር ያመጣብሃል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)