am_tn/pro/25/15.md

966 B

በትዕግስት ገዢን እንዲለዝብ ማድረግ ይቻላል

እነዚህ ቃላት በገቢር ቅርጽ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትእግስተኛ የሆነ ሰው ንጉስን እንዲለዝብ ማድረግ ይችላል” ወይም “ትእግስተኛ ሰው ከንጉስ ጋር መነጋገርና ሃሳቡን ማስለወጥ ይችላል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም ምላስ አጥንትን መስበር ትችላለች

“ምላስ” ሰው ምላሱን በመጠቀም ለሚናገረው ንግግር ምትክ ስም ነው፡፡ “አጥንት” የሚለው ቃል ለጠንካራ ተቃውሞ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልካም ንግግር ጠንካራ ተቃውሞን ማሸነፍ ይችላል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)