am_tn/pro/25/07.md

1.6 KiB

ይልቅ፣ እርሱ “ወደዚህ ና” ቢልህ ይሻላል፡፡

እዚህ ላይ “ና” የሚለው ለንጉሱ ቅርብ የሆነው ጠረጴዛ ወዳለበት ስፍራ ተነስቶ መጠጋት ማለት ነው፡፡ ከንጉሱ አጠገብ መቀመጥ ለአንድ ሰው ትልቅ ክብር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከ … ይልቅ አንድ ሰው ከንጉሱ አጠገብ እንድትቀመጥ ቢጋብዝህ ይሻላል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በተከበሩ ሰዎች ፊት

“በተከበሩ ሰዎች ፊት ለፊት”

ጎረቤትህ ባሳፈረህ ጊዜ በመጨረሻ ምን ታርጋለህ?

ይህ ጥያቄ የተጠየቀው አንባቢው ሁኔታውን በተሳሳተ መንገድ የመረዳት እድል ሊገጥመው እንደሚችል ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡ ጎረቤቱ አንባቢውን ለሃፍረት ሊዳርገው የሚችልበት መንገድ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመጨረሻ ጎረቤትህ ለሃፍረት ከዳረገህ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብህ አታውቅም” ወይም “ጎረቤትህ ማብራሪያ ካለው፣ አንተን ለሃፍረት ይዳርግሃል፣ ከዚያ በኋላ ራስህን ለመከላከል ምንም የምትናገረው ነገር የለህም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)