am_tn/luk/17/01.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢየሱስ ማስተማሩን ቀጥሏል፣ ነገር ግን ንግግሩን ወደ ደቀ መዛሙርቱ መልሷል፡፡ ይህ አሁንም የታሪኩ ተመሳሳይ ክፍል ሲሆን በሉቃስ 15፡3 ላይ የጀመረውን ታሪክ በዚያው ቀን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡

ኃጢአት እንድንሰራ የሚያደርጉ ነገሮች መኖራቸው የተረጋገጠ ነው

"ሰዎች ኃጢአት እንዲሰሩ የሚፈታተኑ ነገሮች በእርግጥ ይፈጠራሉ"

በእርሱ በኩል እነርሱ ለሚመጡበት ለዚያ ሰው

"ፈተናዎች እንዲመጡ ምክንያት ለሚሆን ሰው" ወይም "ሰዎች እንዲፈተኑ ምክንያት ለሚሆን ሰው"

ለእርሱ…ይሻለዋል

ይህ መላምታዊ ሁኔታን ያስተዋውቃል፡፡ ይህ ማለት ይህ ሰው ሰዎች ኃጢአት እንዲሰሩ ምክንያት በመሆኑ የሚደርስበት ቅጣት ባህር ውስጥ ከመስመጥ የከፋ ይሆናል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ቢወረወር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ዙሪያ አስረው ቢወረውሩት" ወይም "በአንድ ሰው አንገት ዙሪያ ከባድ ድንጋይ ተደርጎ ቢወረወር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ…በአንገቱ…እርሱ ይሻለው

እነዚህ ቃላት ሴቶችን እና ወንዶችንም ያመለክታሉ፡፡ (ጡንቻማነት የሚገልጹ ቃላት ሴቶችን ሲያካትት የሚለውን ይመልከቱ)

የወፍጮ ድንጋይ

ይህ በጣም ትልቅ፣ ከባድ ክብ ድንጋይ ሲሆን እህል ለመፍጨት የሚያገለግል ነው፡፡ "ከባድ ድንጋይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እነዚህ ትንንሾች

ይህ እዚህ ስፍራ የሚያመለክተው እምነታቸው ገና ደካማ የሆነውን ነው፡፡ "እነዚህ እምነታቸው ትንሽ የሆነ ሰዎች"

መሰናከል

ይህ ይሁን ሳይባል የሚፈጸምን ኃጢአት የማመልከቻ መንገድ ነው፡፡ "ኃጢአት መፈጸም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡