28 lines
2.3 KiB
Markdown
28 lines
2.3 KiB
Markdown
# የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ?
|
|
|
|
እየሩሳሌምን ለመርዳት ምን ማድረግ እንዳለበት እንዳላወቀ ለማስታወቅ የሚጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የሚጠይቅበት ጥያቄ አይደለም። ጥያቄ ባልሆነ መልኩ ሊጻፍም ይችላል፤ “ልለው የምችለው ነገር የለም. . . እየሩሳሌም”
|
|
|
|
# የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ … ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ
|
|
|
|
ይሄ ቅኔ አዊ የእየሩሳሌም ስም ሲሆን ፣ እዚህ ጋር በሴት ይመስላታል። “ጽዮን” ሌላው የእስራኤል ስም ነው
|
|
|
|
# በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ
|
|
|
|
እየሩሳሌምን ለማጽናናት ምን ማድረግ እንዳለበት እንዳላወቀ ለማስታወቅ የሚጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የሚጠይቅበት ጥያቄ አይደለም። ጥያቄ ባልሆነ መልኩ ሊጻፍም ይችላል፤ “ላወዳድርሽ የምችለው ነገር የለም. . . ጽዮን ሆይ”
|
|
|
|
# ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነው
|
|
|
|
ባህር ታላቅ እንደ ሆነ የእየሩሳሌምም ስብራት እና ሰቆቃ እንዲሁ ነው። “ጉዳትሽ እንደ ባህር ታላቅ ነው”
|
|
|
|
# የሚፈውስሽ ማን ነው?
|
|
|
|
“ማን ይፈውስሻል” ቀድሞ እንደነበረው ሊመልሳት የሚችል ማንም እንደ ሌለ ለመግለጽ የተጠቀመበት መንገድ ነው እንጂ መልስ የሚጠብቅ ጥያቄ አይደለም። በሌላ መልኩም ሊጻፍ ይችላል፤ “ማንም ሊፈውስሽ አይችልም” ወይንም “ማንም ሊመልስሽ አይችልም”
|
|
|
|
# ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም
|
|
|
|
“ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም”። “ምርኮሽን” ይሚለው የሰውን ሃብት እና ብልፅግና ያሳያል።
|
|
|
|
# ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል
|
|
|
|
አይተውልሻል የሚለው ”ተናግረዋል“ በሚለው ሊገለጽ ይችላል። “ከንቱና የማይረባ ነገርንም ተናግረውልሻል”
|