am_tn/isa/50/11.md

822 B

እሳት አንድዳችሁ… የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ

ይህ በጨለማ እየተመላለሱ እንደሆነ ባለፈው ቁጥር የተነገረው ምሳሌ ቀጣይ ነው፡፡ በያህዌ ከመታመን ይልቅ በራሳቸው ጥበብ ለመታመን የሚሞክሩ ሰዎች በጨለማው ውስጥ ማየት እንዲያስችላቸው የራሳቸውን እሳት አንድደው ችቦ እንደያዙ ሰዎች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

በሥቃይ ትጋደማላችሁ

‹‹መጋደም›› የሚያመለክተው መሞትን ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ መሞት በሥቃይ መጋደም ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በታላቅ ሥቃይ ትሞታላችሁ››