am_tn/isa/50/05.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የያህዌ ባርያ መናገር ቀጥሏል፡፡

ጌታ ያህዌ ጆሮዬን ከፍቷል

ያህዌ አገልጋዩን እንዲሰማና እንዲያስተውል መርዳቱ ጆሮውን መክፈት ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ ያህዌ እንድሰማና እንዳስተውል ረዳኝ››

ዐመፀኛ አልነበርሁም፤ ጀርባዬንም አላዞርሁም

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ያህዌ ለሚናገረው አለመታዘዝ እርሱ ላይ ጀርባ ማዞር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ለሚናገረው ታዘዝሁ››

ጀርባዬን ለሚገርፉኝ፣ ጢሜን ለሚነጩ ጉንጩን ሰጠሁ

ሰዎች እንዲገርፉትና ጢሙን እንዲነጩ መፍቀድ ጀርባውንና ጉንጩን ለእነርሱ መስጠት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ጀርባዬን እንዲገርፉኝ፣ ከጉንጬ ላይ ጢሜን እንዲነጩ ፈቀድሁ››

ፊቴን ከውርደትና ከትፋት አልሰወርሁም

ፊትን መሰወር ለራስ መከላከል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሲያፌዙብኝና ሲተፉብኝ ለራሴ አልተከላከልሁም››