2.7 KiB
አጠቃላይ መረጃ
ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡
እኔ ስመጣ ማንም ያልነበረው ለምንድነው? ስጣራ መልስ የሚሰጥ ያልነበረው ለምንድነው?
እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሕዝቡ በምርኮ የተወሰዱት እርሱ እነርሱን ለማዳን ፈቃደኛ ባለ መሆኑ ሳይሆን፣ መልስ ስላልሰጡት መሆኑን ያህዌ አጽንዖት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ስመጣ እዚያ መኖር ሲገባችሁ አልነበራችሁም፤ ስጣራ መመለስ ነበረባችሁ ግን አልመለሳችሁም›› ወይም፣ ‹‹ልናገራችሁ ስመጣ ምላሽ አልሰጣችሁኝም››
እናንተን ለማዳን እጄ አጭር ናትን? ልታደጋችሁ ኀይል የለኝምን?
እነርሱን ለማዳን ዐቅም እንደሌለው በማሰባቸው ሕዝቡን ለመገሠጽ ያህዌ ሁለት ጥያቄዎች አቅርቧል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንተን ለማዳን እጄ በእርግጥ አጭር አይደለችም፤ እናንተን ለመታደግ ኀይል አለኝ›› ወይም፣ ‹‹እናንተን ከጠላቶቻችሁ ለማዳን በእርግጥ ኀይል አለኝ››
እጄ አጭር ናትን?
እዚህ ላይ፣ ‹‹እጄ›› የያህዌን ኀይል ይወክላል፡፡ ያህዌ ዐቅም ከሌለው እጁ አጥራለች ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ በቂ ኀይል የለኝምን?››
ልታደጋችሁስ ኀይል የለኝምን
‹‹እኔ ኀይል የለኝምን?››
ወንዞቹን ምድረ በዳ አደርጋለሁ
ያህዌ ወንዞቹን ማድረቁ እነርሱን ምድረ በዳ ማድረጉ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወንዞቹን እንደ ምድረ በዳ ደረቅ አደርጋለሁ››
ዓሣዎቹም ውሃ በማጣት ሞተው ይገማሉ
‹‹ውሃ ከማጣታቸው የተነሣ ዓሣዎቹ ይሞታሉ፣ ይገማሉ›› - ‹‹የእነርሱ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው ባሕሮችና ወንዞችን ነው፡፡
ሰማዩን ጨለማ አለብሰዋለሁ፤ በማቅ እሸፍነዋለሁ
እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ማቅ የሚያለብሰው ይመስል ሰማዩን ጨለማ እንደሚያደርገው ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥቁር ጨርቅ የለበሰ ይመስል ሰማዩን ጨለማ አደርገዋለሁ፡፡››