1.7 KiB
1.7 KiB
ዕውር… ደንቆሮ የሆነ ሕዝብ
እርሱን የማይሰሙ ወይም የማይታዘዙ ዕውርና ደንቆሮ እንደሆኑ ያህዌ ይናገራል፡፡
ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣ የቀድሞን ነገር ያወጀልን ማን ነው?
ይህ ጥያቄ ሰዎች የሚያመልኳቸውን አማልክት ይመለከታል፡፡ መልሱ ማንም ይህን ማድረግ አይችልም የሚል ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከአማልክቶቻቸው አንዱ እንኳ ይህን መናገርና የቀድሞን ነገር ማወጅ አይችልም››
የቀድሞን ነገር ያወጀልን
ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ነገሮች ከመሆናቸው በፊት ለሰዎች የመነገርን ችሎታ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የቀደሙት ነገሮች ከመሆናቸው በፊት አወጀልን››
ትክክለኛነታቸው እንዲረጋገጥ ምስክርቻቸውን ያቅርቡ፤ ሰምተውም ያረጋግጡላቸው ‹እውነት ነው›
ምንም እንኳ ያንን ማድረግ እንደማይችሉ ቢያውቅም፣ አሕዛብ የሚያመልኳቸው አማልክት እነዚህን ነገሮች ማድረግ እንደሚችሉ የሚያረጋግጡ ምስክሮች እንዲያቀርቡ ያህዌ ይጠይቃል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነዚህ አማልክት ትክክል መሆናቸውን የሚመሰክሩ ምስክሮች አድምጠውም፣ ‹እውነት ነው› የሚሉ ምስክሮች የሏቸውም››