1.6 KiB
1.6 KiB
ወደ ተርሴስ ተሻገሩ
"ጉዞአችሁን ወደ ተርሴስ አድርጉ፡፡' ተርሴስ፣ የጢሮስ ሰዎች ለንግድ ጉዞ የሚያደርጉባት ሩቅ ቦታ ነች፡፡ ከጢሮስ ላመለጡ ብቸኛ የድኅንነት ቦታ ነች፡፡
በቀድሞ ዘመን ተመሥርታ የነበረችው፣ … ደስተኛይቱ ከተማ፣ ይህ ደረሰባትን
እግዚአብሔር በጢሮስ ላይ ለመሳለቅ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በአሳብ ገላጭ አረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ለመደላደል … በጥንታዊቷ የጢሮስ ከተማ በሙሉ ደስታ የምትኖሩ በእርግጥ ይህ ይደርስባችኋል' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ደስተኛይቱ ከተማ
በዚህ ስፍራ "ከተማ' የሚለው ሕዝቡን ይወክላል፡፡ አት፡- "በጢሮስ ከተማ የሚኖር ደስተኛ ሕዝብ' (ምትክ ስም ተመልከት)
ለመደላደል እግሮችዋ ወደ ሩቅ ወደ እንግዳ ሥፍራዎች የወሰዷት
በዚህ ስፍራ "እግር' መላውን የሰው ማንነት ይወክላል፡፡ አት፡- "ለመኖርና ገንዘብ ለማትረፍ ወደ ሩቅ ስፍራዎች የሄዱ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
ወደ ሩቅ … የወሰዷት
በዚህ ስፍራ "የወሰዷት' የሚለው የጢሮስን ሕዝብ የምትወክለውን የጢሮስን ከተማ ያመለክታል፡፡ (ምትክ ስም ተመልከት)