am_tn/2sa/15/35.md

1.5 KiB

ካህናቱ ሳዶቅ እና አብያታር ከአንተ ጋር አይደሉምን?

ዳዊት ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው ኩሲ ብቻውን እንደማይሆን ሊነግረው ፈልጎ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ካህናቱ ሳዶቅ እና አብያታር አንተን ለመርዳት በዚያ ይገኛሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የምትሰማውን ሁሉ

ይህ አጠቃላይ አስተያየት ነው፡፡ ይህ ማለት ማናቸውንም ጠቃሚ እና መረጃ ሊሆኑ የሚችሉ የሚሰማቸውን ነገሮች ማለት እንጂ እያንዳንዷን ቃል ማለት አይደለም፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

አኪማአስ…ዮናታን

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በእጃቸው

"እጃቸው" የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው ወጣት ወንዶችን ሲሆን እነርሱም መልዕክተኛ ሆነው ያገለግላሉ ማለት ነው፡፡ "ልጆቻቸው ለእኔ እንዲነግሩኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)