am_tn/zep/03/19.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

3፥19-20 ላይ ሶፎንያስ በቀጥታ ከፍርድ የተረፉ የእስራኤል ትሩፋን ደስ እንዲሰኙ ይናገራል፡፡

እነሆ

ይህ የሚያመለክተው አንባቢው ለሚከተለው ትኩረት እንዲሰጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተመልከቱ›› ወይም፣ ‹‹ልብ በሉ››

ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ

ይህም፣ ‹‹አንቺን ያስጨነቁትን በእርግጥ እቀጣቸዋለሁ›› ማለት ነው፡፡

አንካሶችን እታደጋለሁ፤ የተበተኑትንም እሰበስባለሁ

በምርኮ የነበሩት እስራኤላውያን አንካሶችና የተበተኑ እንደ ነበሩ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ አንካሶችና እንደ ተበተኑ ሰዎች የሆኑትን የእስራኤል ትሩፋን እታደጋለሁ››

አንካሳ

መራመድ የማይችል ሰው ወይም እንስሳ

ለውዳሴና ለክብር አደርጋቸዋለሁ

እዚህ ላይ የተሟላ ሐሳቡ፣ ‹‹የምስጋና ምክንያት አድርጋቸዋለሁ›› ማለትም፣ ‹‹ሌሎች ያመሰግናቸዋል››

ውርደታቸውን ወደ ዝና እለውጣለሁ

ውርደትና ዝና እንደ ድርጊት ሊነገሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ሰዎች እንዲያከብሯቸው እንጂ፣ እንዲያፍሩ አላደርግም››

በዚያ ጊዜ እመራችኋለሁ፤ በዚያ ጊዜ በአንድነት እሰበስባችኋለሁ፡፡

እነዚህ ሁለት ሐረጐች የሚናገሩት ስለ ተመሳሳይ ነገር ሲሆን፣ በምርኮ ያሉ ሰዎችን ያህዌ ወደ ትውልድ አገራቸው እንደሚያመጣ ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚያ ጊዜ በአንድነት ሰብስቤ ወደ ትውልድ አገራችሁ አመጣችኋለሁ››