am_tn/zep/03/14.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

3፥14-20 ላይ ሶፎንያስ ደስ እንዲላቸው ከፍርድ ለተረፉ ትሩፋን ይናገራል፡፡

የጽዮን ልጅ… የኢየሩሳሌም ልጅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ልጅ›› በከተማው የሚኖሩትን ሁሉ ይመለከታል፡፡

ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ

ሁለቱም ሐረጐች አንድ ዐይነት ትርጒም ቢኖራቸውም፣ ምን ያህል ደስ ሊላቸው እንደሚገባ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ደስ ይበላችሁ››

በፍጹም ልብሽ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ልብ›› የሰውን ውስጣዊ ሁለንተና ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍጹም ሁለንተናሽ››

ያህዌ ቅጣትሽን አስወግዶአል

ቅጣትን ማስወገድ ቅጣትን መተው ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ያህዌ አንቺን መቅጣቱን ትቶአል››

ከእንግዲህ ወዲያ አንዳች ክፉ ነገር አትፈሪም

‹‹ክፉ›› የሚለው ድርጊትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎች ይጐዱኛል ብለሽ አትፈሪም››

በዚያ ቀን

‹‹በዚያ ቀን›› ወይም፣ ‹‹ያ በሚሆንበት ጊዜ›› ይህ የሚያመለክተው የያህዌን ቀን ወዲያውኑ ተከትሎ የሚመጣውን የሰላምና የመታደስ ጊዜ ነው፡፡

ለኢየሩሳሌም… ለጽዮን እንዲህ ይሏታል

ስሞቹ የሚያመለክቱት እዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ነው፡፡ ‹‹ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ለጽዮን ሕዝብ እንዲህ ይላል››

እጆችሽ አይዛሉ

ደካማና ዐቅም ቢስ መሆን በእጆች መዛል ተመስሎአል፡፡ እዚህ ላይ ‹‹እጆች›› የሰውን ሁለንተና ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አትድከሚ››