am_tn/zep/03/12.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

3፥11-13 ላይ ያህዌ ከፍርድ የተረፉ የእስራኤል ትሩፋንን ያጽናናል፡፡

የዋሃንንና ትሑታንን በመካከላችሁ አስቀራለሁ… የእስራኤልን ትሩፋን

በመጀመሪያው ሐረግ፣ ‹‹ትሩፋኑን›› በሁለተኛው ሐረግ አስቀምጦአል፡፡

የያህዌን ስም መጠጊያ ያደርጋሉ

ያህዌ ለእነዚህ ትሩፋን የሚያደርገው ጥበቃ እርሱ መጠጊያ ወይም መጠለያ ከመሆኑ ጋር ተመሳስሎአል፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹የያህዌ ስም›› ማንነቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ያህዌ ይመጣሉ፤ እርሱም ይረዳቸዋል››

ኀጢአት አይሠሩም

‹‹ክፉ ነገር አያደርጉም››

ምላሳቸውም ሐሰት አይናገርም፤ በአንደበታቸውም ተንኰል አይገኝም

‹‹ምላስ… በአንደበታቸው›› የሚለው ምላስ አንደበት እንዲናገር የሚያደርገውን ነገር ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንኛቸውም ክፉ ነገር አይናገሩም›› ወይም፣ ‹‹ክፉ ነገር አያወሩም››

ይበላሉ ይተኛሉ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝቡ ስለሚያደርገው ቸርነት ሲናገር እነርሱ በሰላም ተመግበው የሚያርፉ በጐቹ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡