am_tn/zep/03/09.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

3፥9-10 ላይ ያህዌ ከፍርድ በኃላ ሕዝቦችን እንደሚያድስ ይናገራል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

3፥11-13 ላይ ያህዌ ከፍርድ የተረፉ ትሩፋንን ያጽናናል፡፡

አንደበታቸውን አጠራለሁ

‹‹አንደበት›› የመናገር ችሎታን ያመለክታል፡፡ ‹‹ሕዝቡ እውነትን›› እንዲናገሩ አደርጋለሁ››

የያህዌን ስም እንዲጠሩ

ይህ ያህዌን ያመልካሉ ለማለት ጥቅም ላይ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌን እንዲያመልኩ››

ተስማምተው እንዲያገለግሉ

‹‹ተስማምተው›› በአንድነት ሆነው ማለት ነው፡፡

ከኩሽ ወንዞች ማዶ

ይህ የሚያመለክተው በዚህ ዘመን ሱዳን ያለችበትን ሊሆን ይችላል፡፡

በዚያ ቀን… በዚያ ጊዜ

‹‹በዚያ ጊዜ… ያ ሲሆን›› ይህ የሚያመለክተው የያህዌን ቀን ወዲያውኑ ተክትሎ የሚኖረውን የሰላምና የመታደስ ጊዜ ነው፡፡

በዚያ ቀን ባደረጋችሁት አታፍሩም፡፡

ይህ ድርጊትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ባደረጋችሁ ነገር ከእንግዲህ በፍጹም አታፍሩም››

በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን

‹‹በጣም የሚታበዩ ሰዎች ሁሉ››