am_tn/zep/03/06.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

3፥6-7 ሌሎች ኀጢአተኞች ከተሞች ላይ እንዴት እንደ ፈረደ ባለ መማራቸው ያህዌ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ይገሥጻል፡፡ ይህን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ቁጥር 6 መጀመሪያ ላይ ያህዌ እንዲህ ይላል የሚል መጨመር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡

ማንም እንዳያልፍባቸው መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል አንድም ሰው የለም፡፡

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች የሚናገሩት ስለ አንድ ጉዳይ ሲሆን፣ የከተማዎቹ መደምሰስ እርግጥ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡

ማንም እንዳያልፍባቸው

‹‹ማንም አያልፍባቸውም››

ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም

‹‹እዚያ ማንም አይኖርም›› — ይህን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ ‹‹ሁሉም ይሞታሉ›› ማለት ይቻላል፡፡

እኔም፣ ‹‹ትፈሪኛለሽ… ቅጣቴም በእርሷ ላይ አይደርስም ብዬ ነበር፡፡››

እኔን ይፈሩኛል፤ አስቀድሞ እንዳልሁት ከቤቶቻችው እንዳይነቀሉ እርምት ይቀበላሉ ብዬ ነበር፡፡››

ከቤታቸውም አይቆረጡም

እዚህ ላይ፣ ‹‹አይቆረጡም›› የሚለው መወገድን ያመለክታል፡፡ ይህንንም፣ ‹‹ከቤታቸው እንዳላስወግዳቸው›› ማለት ይቻላል፡፡

ክፋትን በመፈጸም እየተጉ ሄዱ

‹‹ክፉ ነገሮችን በማድረግ››