am_tn/zep/02/15.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

2፥4-15 ላይ ያህል በይሁዳ ዙሪያ ባሉ አገሮች ላይ የሚመጣውን ፍርድ ይናገራል፡፡

ደስተኛዪቱ ከተማ

‹‹በራስዋ የምትኮራ ከተማ›› ይህ የሚያመለክተው ሶፎንያስ 2፥13 ላይ ያህዌ ስለ እርሷ መናገር የጀመረውን የነነዌን ከተማ ነው፡፡

በልቧ… ያለች

አባባሉ፣ ‹‹ለራስዋ አለች›› ወይም፣ ‹‹አሰበች›› ማለት ነው፡፡ ስለ ከተማዋ የሚናገረው መናገር እንደሚችል ሰው አድርጐ ነው፡፡ በዚያ ከተማ የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡

እኔ ብቻ ነኝ ከእኔ በቀር ማንም የለም

እኔ ብቻ ነኝ ያለችበትን ምክንያት መግለጹ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ታላቋ ከተማ ነኝ፤ ከእኔ የሚወዳደር የለም››

አስፈሪ

‹‹ለማየት የሚያስፈራ ቦታ››

ያፌዙባታል እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል

ፌዝ ጮኽ ያለ ድምፅ ነው፡፡ ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ሰዎች ነነዌ ላይ በጣም መቆጣታቸውን ነው፡፡