am_tn/zep/02/08.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

2፥4-15 ላይ ያህዌ በይሁዳ ዙሪያ ባሉ አገሮች ላይ ስለሚመጣው የእርሱ ፍርድ ይናገራል

ፌዝ… ስድብ

‹‹ፌዝ… ስድብ›› የተሰኙት ሁለት ሐረጐች የሚናገሩት ስለ አንድ ዐይነት ነገር ሲሆን፣ ሞዓብና አሞን ያህዌን መሳደባቸውን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡

ድንበራቸውን አልፈዋል

ይህ የሚያመለክተው እነርሱን ለማጥቃት የይሁዳን ክልል መሻገራቸውን ሊሆን ይችላል

በሕያውነቴ

‹‹እኔ ሕያው እንደ መሆኔ›› ያህዌ በዚህ አገላለጽ የሚጠቀመው ቀጥሎ የሚናገረው ፍጹም እውነት መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡

ይህ የመሐላ ቃል ነው፡፡ ‹‹አጥብቄ እምላለሁ›› ይህ የሰራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ የያህዌ ቃል ነው

የሚናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳየት ያህዌ ስሙን በመጥራት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹የሰራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ያህዌ እንዲህ ይላል›› ወይም፣ ‹‹እኔ የሰራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ ያህዌ ይህን ተናግሬአለሁ››

እንደ ሰዶም… እንደ ገሞራ

እነዚህን ሁለት ከተሞች በጣም ዐመፀኞች ስለ ነበሩ ከሰማይ በወረደ እሳት አጥፍቶአቸዋል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን ነው፡፡ ይህን ግልጽ በሆነ ሁኔታ፣ ‹‹እንደ ሰዶም… እንደ ገሞራ ሙሉ በሙሉ አጥፍቶአቸዋል›› ብሎ መተርጐም ይቻላል፡፡

ዐረም እንደ ዋጠው እንደ ጨው ጉድጓድ

‹‹እሾህ የሞላበት የጨው ጉድጓድ›› ይህ የሚያመለክተው ጠፍና ጥቅም የሌለውን ምድር ነው፡፡

ከሕዝቤ የቀሩ… ከወገኔ የተረፉ

ሁለቱም ሐረጐች የሚናገሩት ስለ ተመሳሳይ ነገር ሲሆን፣ እስራኤላውያን ከያህዌ ቅጣት እንደሚተርፉ ያመለክታሉ፡፡