am_tn/zep/02/04.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

2፥4-15 ላይ ያህዌ በይሁዳ ዙሪያ ባሉ አገሮች ላይ ስለሚመጣው የእርሱ ፍርድ ይናገራል፡፡

ጋዛ… አስቀሎና… አሽዶድ… አቃሮን

እነዚህ በዚያ ዘመን የነበሩ አራቱ የፍልስጥኤም ከተሞች ናቸው፡፡

ባድማ ይሆናሉ… ይፈራርሳሉ

የእነዚህ ሁለት ሐረጐች ትርጉም ተመሳሳይ ሲሆን፣ እነዚህ ከተሞች ሙሉ በሙሉ እንደሚጠፉ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

አሽዶድ በቀትር ትባረራለች

እዚህ ላይ ‹‹እነርሱ›› የሚለው የፍልስጥኤማውያንን ጠላቶች ነው፡፡ ‹‹ቀትር›› ለሚለው አማራጭ ትርጒም፣ 1) ጠላቶች አሽዶድን ከቀትር በፊት ድል ያደርጓታል፤ ወይም 2) ሕዝቡ ዕረፍት ላይ እያሉና ምንም ሳያስቡ ጠላቶች አሽዶድን በቀትር ያጠቋታል የሚል ሊሆን ይችላል፡፡

አቃሮንም ትነቀላለች

የአቃሮን መሸነፍ ከመሬት ተነቅሎ በሚጣል ዛፍ ተመስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአቃሮንን ሰዎች ዛፍ ከሥሩ እንደሚነቀል ይነቅሏቸዋል›› ማለት ለሆን ይችላል፡፡

በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ የከሊታውያን ሰዎች

የመጀመሪያው ሐረግ ከሊታውያን የሚኖሩበትን ይመለክታል፡፡

የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን

ፍልስጥኤማውያን በከነዓን ከሚኖሩ ሕዝቦች አንዱ ነበሩ

ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም

‹‹ምንም እስከማይተርፍ ድረስ›› - ይህ፣ ‹‹ነዋሪዎቿ ሁሉ ይሞታሉ›› ተብሎ ሊተረጐም ይችላል፡፡