am_tn/zep/02/01.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

2፥1-3 ላይ ያህዌ ለይሁዳ መናገሩን ቀጥሏል፤ ንስሐ እንዲገቡ ይነግራቸዋል፡፡

በአንድነት ተሰብሰቡ

እነዚህ ሁለት ቃሎች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በኀጢአታቸው ንስሐ ለመግባት ሰዎች በአንድነት እንዲሰበሰቡ የተሰጠውን ትእዛዝ ያጠናክራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ››

እፍረት የሌላችሁ ሕዝብ

ሕዝቡ በኀጢአታቸው አላዘኑም

የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ

ይህ ያህዌ በወሰነው ጊዜ የሚመጣውን ቅጣት ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ እናንተን ከመቅጣቱ በፊት››

ያ ቀን… የያህዌ ጽኑ ቁጣ… የያህዌ የመዐት ቀን

እነዚህ ሐረጐች ሁሉም የሚያመለክቱት፣ ‹‹የያህዌ ቀን››ን ነው፡፡ እነዚህን ሐረጐች ሶፎንያስ 1፥7-9 ላይ ተመሳሳይ ሐረጐችን በተረጐምህበት ሁኔታ ተርጉማቸው፡፡

ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ

ገለባ ነፋስ ጠርጐ የሚወስደው የማያስፈልግ የፍሬው አካል ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የፍርድ ቀን ቶሎ ይመጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ገለባ በነፋስ እንደሚጠረግ ያ ቀን በፍጥነት ይመጣል፡፡

የያህዌ ጽኑ ቁጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፤ የያህዌ የመዓት ቀን ሳይደርስባችሁ››

የያህዌ ፍርድ ምን ያህል ከባድ መሆኑን ለማመልከትና ሰዎች በአስቸኳይ ንስሐ እንዲገቡ አጽንዖት ለመስጠት ነቢዩ በጣም የሚመሳሰሉ ሐረጐች ተጠቅሟል፡፡

የያህዌ ቁጣ

ይህ የእግዚአብሔርን ቅጣት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያህዌ ቅጣት››

ያህዌን እሹ

ያህዌን መሻት፣ 1) የእግዚአብሔርን ርዳታ መለመንን ወይም 2) ስለ እግዚአብሔር ማሰብንና ለእርሱ መታዘዝን ይወክላል፡፡

ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ

‹‹ጽድቅ›› እና፣ ‹‹ትሕትና›› የተሰኙት ድርጊትን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ትክክል የሆነውን ለማድረግና ትሑት ለመሆን ፈልጉ››

በያህዌ የቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል

ይህን፣ ‹‹በቁጣው ቀን ያህዌ ይሰውራችኃል›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡