am_tn/zep/01/17.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

1፥2-18 የያህዌን ፍርድ ያመለክታል፡፡ 1፥17-18 በእያንዳንዱ ኀጢአተኛ ላይ ወደ ፊት የሚመጣውን የመጨረሻ የያህዌ ፍርድ ያመለክታል፡፡

እንደ ዕውር እንዲራመዱ

ከያህዌ ፍርድ የተነሣ ሰዎች ግራ ይጋባሉ፤ እነርሱ ሲራመዱ የሚመለከቱ ሰዎች ዕውር እንደ ሆኑ ያስባሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐይናቸው እንደ ታወረ ሰዎች ግራ በመጋባት ይመላለሳሉ››

ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል

የሚፈሰሰው ደማቸው እንደ ትቢያ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ይህን፣ ‹‹የሚፈስሰው ደማቸውን ጠላቶቻቸው እንደ ትቢያ ይቆጥሩታል›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡

ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይጣላል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ይፈስሳል›› የሚለው ግልጽ ሆኗል፡፡ ይህን፣ ‹‹ጠላቶቻቸው ሥጋቸውን ይቆርጣሉ፤ እንደ ጉድፍ እንዲበሰብስም ያደርጋሉ›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡

የቅንዓቱ እሳት

‹‹እሳት›› የያህዌን ቁጣ ከባድነት ያመለክታል፡፡ ይህን፣ ‹‹ቅንዓቱ እንደ ታላቅ እሳት ነው›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡

በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ

ይህ የሚያመለክተው ዐመፀኞችን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህንን፣ ‹‹በምድር የሚኖሩ ዐመፀኞች ሁሉ›› በማለት የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡