am_tn/zep/01/14.md

3.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሶፎንያስ 1፥2-18 የያህዌን ፍርድ ያመለክታል፡፡ ቁጥር 1፥4-16 በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚመጣውን የያህዌ ፍርድ ያመለክታል፡፡

ቅርብ ነው፤ ቅርብ ነው፤ ፈጥኖም ይመጣል

‹‹ቅርብ›› የሚለው ቃል መደጋገምና፣ ‹‹ፈጥኖም ይመጣል›› የሚለው ሐረግ ያህዌ ሕዝቡ ላይ የሚፈርደው በቅርቡ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ‹‹ሳይውል ሳያድር ቶሎ ይሆናል››

የያህዌ ቀን

ሶፎንያስ 1፥7 የተረጐምህበትን ሁኔታ ተመልከት፡፡

ጦረኛው ምርር ብሎ ይጮኻል

አማራጭ ትርጒሙ 1) ተስፋ በመቁረጥ የሚጮኽ ወታደር፤ ወይም 2) የወታደር የጦርነት ጩኸት ሊሆን ይችላል፡፡

ያ ቀን… ቀን

እነዚህ ቃሎች ቁጥር 14 ላይ ያለውን፣ ‹‹የያህዌ ቀን›› ያመለክታሉ፡፡

ያ ቀን የመዓት ቀን የውጊያ ቀን

ቁጥር 15-16 በአንድነት ሆነው ስለዚህ የመጨረሻ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚያስከትለው ከባድ ጥፋት አጽንዖት የሚሰጡ የተለያዩ የአነጋገር መንገዶች አሉት፡፡

የመከራና የጭንቀት ቀን

‹‹መከራ›› እና ‹‹ጭንቀት›› የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት ስለ ተመሳሳይ ነገር ቢሆንም፣ ስለ ሕዝቡ ጭንቀት ከባድ መሆን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ ‹‹ሰዎች ከባድ ጭንቀት ውስጥ የሚሆኑበት ቀን››

የሁከትና የጥፋት ቀን

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሁከት›› የሚያመለክተው መለኮታዊ ፍርድን ነው፡፡ ‹‹ጥፋት›› የሚለው ቃል የዚያን ፍርድ ውጤት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አውዳሚ የሁከት ቀን›› ወይም፣ ‹‹አውዳሚ ፍርድ››

የጨለማና የጭጋግ ቀን

‹‹ጨለማ›› እና ‹‹ጭጋግ›› ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፤ የጨለማውን ከባድነት ያመለክታል፡፡ ሁለቱም የሚያመለክቱት የጥፋት ወይም የመለኮታዊ ፍርድን ጊዜ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጨለማ የዋጠው ቀን›› ወይም ‹‹አስፈሪ የፍርድ ቀን››

የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን

ይህኛውም የሚናገረው ስለ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የነበረውን ሐረግ ሐሳብ ያጠናክራል፡፡ ‹‹ደመና›› እና፣ ‹‹ድቅድቅ ጨለማ›› የተሰኙትን የመሳሰሉ ሐረጐች መለኮታዊ ፍርድን ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥቁር ደመና የሞላበት ቀን››

የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን

‹‹መለከት›› እና፣ ‹‹የጦርነት ጩኸት›› የተሰኙት ቃሎች እዚህ ላይ የሚያሳዩት ተመሳሳይ ነገርን ነው፡፡ ሁለቱም ወታደሮች ለጦርነት እንዲዘጋጁ መጥሪያ መንገዶች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች የጦርነት ጥሪ የሚያሰሙበት ቀን››

በተመሸጉ ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ

ሁለቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት ወታደራዊ ምሽጐችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሚገባ የተመሸጉ ከተሞች››