am_tn/zep/01/10.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 1፥2-18 የያህዌን ፍርድ ያመላክታሉ፡፡ ቁጥር 1፥4-16 በይሁዳ ላይ የያህዌን ፍርድ ያመለክታሉ፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 1፥8-13 ላይ ያህዌ ይናገራል፡፡ የሚናገረው የመጀመሪያ መጠሪያን በመጠቀምና ስለ ራሱ በሦስተኛ መጠሪያ በመናገር ነው፡፡

በዚያን ቀን

‹‹የያህዌ ቀን›› ሶፎንያስ 1፥9 የተረጐምህበትን ሁኔታ ተመልከት፡፡

የያህዌ አነጋገር

እየተናገረ ያለው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳየት ያህዌ ስሙን በመጥራት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ‹‹ያህዌ የተናገረው›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ በመሐላ የተናገረው››

የዓሣ በር

የዓሣ በር በኢየሩሳሌም ከተማ ግንብ ከነበሩ በሮች አንዱ ነው፡፡

በሁለተኛው አደባባይ ዋይታ

‹‹በሁለተኛው አደባባይ… ዋይ በሉ፡፡›› ‹‹ሁለተኛው በር›› አዲሱ የኢየሩሳሌም ክፍል ነው፡፡

ታላቅ ሽብር ይሰማል

ይህ የሚያመለክተው ግንቡ ሲወድቅ የሚሰማውን ጩኸት ነው፡፡ ይህን፣ ‹‹ግንቡ ሲወድቅ የሚኖረው ታላቅ ድምፅ›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡

ከኮረብቶችም

ይህ የሚናገረው ኢየሩሳሌም ዙሪያ ስላሉት ኮረብቶች ነው፡፡

ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ፡፡

እነዚህ ሁለት ሐረጐች የሚናገሩት ስለ አንድ ሕዝብ ሲሆን፣ ንግዳቸው እንደሚጠፋ አጽንዖት ለመስጠት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ‹‹ዕቃዎችን የሚገዙና የሚሸጡ ይገደላሉ፡፡››

በብር የሚነግዱ

ይህ የሚመለከተው ነጋዴዎችን ነው፡፡ ሳንቲሞች ከመሠራታቸው በፊት ለገዙት ዕቃ ለመክፈል ሰዎች ብርና ወርቅ ይመዝኑ ነበር፡፡

ይደመሰሳሉ

አንድን ነገር ከአካሉ ቆርጦ መጣልን በሚያመለክት ሁኔታ ይደመሰሳሉ በሚለው ቃል ተጠቅሞአል፡፡ ይህን ሶፎንያስ 1፥3 ላይ ከተረጐምህበት ሁኔታ ተመልከት፡፡ ‹‹አጠፋለሁ››