am_tn/zep/01/07.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 1፥2-18 የያህዌን ፍርድ ያመለክታል፡፡ ቁጥር 1፥4-16 በይሁዳ ሕዝብ ላይ የያህዌን ፍርድ ያሳያል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 1፥8-13 ላይ ያህዌ ሲናገር እንመለከታለን፡፡ ስለ ራሱ ሲናገር በመጀመሪያና በሦስተኛ ሰው ይጠቀማል፡፡

ዝም በሉ

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ እዚህ ላይ ዝምታ የድንጋጤና የመደነቅ ምልክት ነው፡፡ ‹‹ደንግጡ››

ያህዌ መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤ እንግዶቹንም ቀድሶአል

የይሁዳ ሰዎች እንደ ያህዌ መሥዋዕት ጠላት የሆኑት ሕዝብ መሥዋዕቱን እንደሚበሉ የእርሱ እንግዶች ተገልጠዋል፡፡ በጣም ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይህ፣ ‹‹ያህዌ የይሁዳን ሕዝብ እንደ መሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤ ጠላት የሆኑትን ሕዝብ በእንግድነት ጠርቷል›› ሊባል ይችላል፡፡

እንግዶቹንም ቀድሶአል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ቀድሶአል›› ወደ ግብዣ ጠርቷል ለማለት ጥቅም ላይ የዋለ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡

አዘጋጅቶአል

ይህ ቃል ይሁዳ ላይ የያህዌ ፍርድ የሚጀመርበትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ

ለባሕላቸው ያላቸውን ፍቅርና ባዕዳን ጣዖቶቻቸውን ማምለካቸውን ለማሳየት እስራኤላውያን ከባዕዳን ጋር የሚመሳሰል ልብስ መልበሳቸውን የሚያመለክት ሐረግ ነው፡፡ ‹‹ባዕዳን ጣዖታትን የሚያመልኩ ሁሉ››

በዚያን ቀን

‹‹በያህዌ ቀን››

በመድረኩ ላይ የሚዘሉትን ሁሉ

አማራጭ ትርጒሞቹ፣ 1) ይህ ዳጐን የሚባለውን ለማምለክ መድረኩ ላይ የዘለሉትን ሰዎች የሚያመለክት ነው፤ ወይም 2) የአረማውያንን አማልክት ለማምለክ መድረኩ ላይ የዘለሉትን ሰዎች ያመለክታል፤ ወይም 3) ወደ ዙፋን የወጡ ንጉሣውያን ባለ ሥልጣኖች ያመለክታል፡፡

የአማልክቶቻቸውን ቤት በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ

‹‹ዐመፅ›› እና ‹‹ማጭበርበር›› የተሰኙት ድርጊትን ያመለክታሉ፡፡ ‹‹ዐመፅ የሚያደርጉና በአማልክቶቻቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚዋሹትን እቀጣለሁ፡፡››